Skip to content
Victorian Government Website (Victoria, the Place to Be)
Department of Human Services, Victoria, Australia
Disability Services

Information in Community Languages - Amharic

በማህበረሰብ/በኮሙኒቲ ቋንቋዎች የቀረበ መረጃ

ሰዎች በሚኖራቸው ባህል፣ ችሎታ፣ እድሜ ወይም ፆታን ሳይለዩ፣ በቪክቶሪያ ሁሉም እንደ ፍላጎቱ የሚኖርበት ቦታ እንድትሆን የቪክቶሪያ መንግሥት ፍላጎት ነው። ለእያንዳንዱ ሰው አግባብ ያለው እርዳታና አገልግሎት በአካለስንኩላን አገልግሎት በኩል እንዲቀርብ የቪክቶሪያ አስተዳደር ከ 2002 እስከ 2012 ዓ.ም ለአካለስንኩላን እቅድ በማውጣት (Victorian State Disability Plan 2002-2012) እንደ አንዱ የወደፊት ሀሳብ ይሆናል።

እርዳታ ሊቀርብ የሚችለው፡

  • በቤትዎ ውስጥ ሲኖሩ
  • በማህበረሰብዎ ተሳታፊ ሲሆኑ
  • ለቤተሰብ እና ተንከባካቢዎች ይሆናል።

በዚህ እርዳታ የሚካተቱ፡

  • ለማህበረሰቡ በሚሰጡ እርዳታዎች ማለት እንደ ከርስዎ የከተማ ምክር ቤት፣ ከማህበረሰብ ጤና ጥበቃ ማእከል ወይም ከጎረቤታሞች (ኔይበርሁድ ሃውስ) አገልግሎቶች
  • ልዩ የአካለስንኩል እርዳታ
  • መኖሪያ ቤት

አካለጎደሎ ለሆኑ ሰዎችና ተንከባካቢዎቻቸው ስለሚቀርቡ እርዳታዎችና አገልግሎቶች የአካለስንኩል ያዥና ተጠያቂ አገልግሎት (Disability Intake and Response Service) መረጃ ማቅረብ ይችላል። እንዲሁም ይህ አገልግሎት አካለጎደሎ ለሆኑ ሰዎች፣ ለቤተሰባቸው እና ለተንከባካቦዎቻቸው እቅድና እርዳታ በአካባቢያቸው እንዲቀርብላቸው ይረዳሉ።

በአካባቢዎ ስለሚገኝ እርዳታና አገልግሎት በተመለከተ ለሆነ ሰው ለማነጋገር ከፈለጉ በአስተዳደር ግዛትዎ ያለውን የአካለስንኩል ያዥና ተጠያቂ አገልግሎት (Disability Intake and Response Service) መጠየቅ ነው።

አስተርጓሚ ይፈልጋሉን?

እባክዎ የአስተርጓሚ አገልግሎትን በ 13 14 50 በመደወል በግዛትዎ አግባብ ባለው የአካለስንኩል ያዥና ተጠያቂ አገልግሎት (Disability Intake and Response Service) ስልክ ቁጥር ላይ እንዲገናኙ ስልከኛውን መጠየቅ ይሆናል።

ለመረጃ የቀረቡ ፅሁፎች

በፅሁፍ ከተዘጋጀው መረጃ ባሻገር በሌላ አማራጭ ከፈለጉ ወይም የተያያዘውን ፅሁፍ ለመክፈት ችግር ካለብዎ በኢሜል፡ (disability.services@dhs.vic.gov.au) የአካለጎደሎ አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቻላል።

በተዛመደ ጉዳይ መረጃ ለማግኘት

  • በመስመር ላይ እያሉ ለአካለጎደሎ አገልግሎት ማውጫ (Disability Online Service Directory) - በራስዎ ቋንቋ የቀረቡ አገልግሎቶችን መፈለግ
  • በጤና ጥበቃ ለተተረጎመ ማውጫ (Health Translations Directory) - ከእንግሊዝኛ ባሻገር በሌላ ቋንቋ የተተረጎሙ የጤና ጥበቃ መረጃ መመሪያ